ብቁ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር በወጣቶች ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ብቁ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር በወጣቶች ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች በስብዕና እና በሥነ-ምግባር ታንጸው፣ ብቁ ሀገር ተረካቢ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በምክር ቤት ጉባኤ ላይ እንደገለጹት፣ ከተማ አስተዳደሩ ወጣቱን ከሱስና ካልተገባ ሥነ-ምግባር ለመታደግ ስፖርትን እና ኪነ-ጥበብን እንደ ዋነኛ መሣሪያ ተጠቅመናል ብለዋል፡፡

ወጣቶች ያላቸውን ተሰጥኦ እንዲያወጡ እና መለማመድ የሚያስችሉ 115 ፕላዛዎች እና 53 አንፊቲያትሮች ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አክለውም በስፖርቱ ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ታሳቢ ያደረጉ 4 ግዙፍ ስታዲየሞች እንዲኖሩ ታሳቢ ተደርጎ መሰራቱን አንስተው፣ በየሰፈሩም የስፖርት ሜዳዎች በስፋት እየተስፋፉ ይገኛሉ ብለዋል።

በስፖርቱ ዘርፍ ውጤታማ ወጣቶችን ለማፍራት ከ 3 ሺህ በላይ ወጣቶች ልዩ ድጋፍና ስልጠና እየተሰጣቸው እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡

ባለፉት 3 ዓመታት ብቻ 5 ሺህ የልጆች መጫወቻዎች እና 1,100 የሕፃናት ማቆያዎች መገንባታቸውንም አብራርተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አክለውም፣ አዲስ አበባ በሕፃናትና ወጣቶች ልማት ዙሪያ ያከናወነቻቸው ተግባራት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ መሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በስፖርቱና በኪነ ጥበቡ ዘርፍ ለሀገር አሰባሳቢ ትርክት በመስራት ታላቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለሙያዎችን እውቅና ችረናቸዋል፣ ይህም ወጣቱ ትውልድ የእነሱን አሻራ በመከተል ለሀገር እና ለወገኝ አኩሪ ስራ ለመስራት እንዲነሳሳ ያደርገዋል ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review