አዲስ አበባ የመጀመሪያውን አህጉራዊ የቀዳማይ ልጅነት ጉባኤ ልታስተናግድ ነው

You are currently viewing አዲስ አበባ የመጀመሪያውን አህጉራዊ የቀዳማይ ልጅነት ጉባኤ ልታስተናግድ ነው

AMN – ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም

የ19 ሀገራት ተወካዮች የሚሳተፉበት የመጀመሪያው አዲስ አፍሪካ ቀዳማይ ልጅነት ጉባኤ ከግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ጉባኤው “አፍሪካ በቀዳማይ ልጅነት ሥርዓት ለውጥ የግንባር ቀደምትነት ሚና ፤ ከአካባቢያዊ ሞዴሎች ወደ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን፣ የአፍሪካ ሀገራትን የፖሊሲ አቅጣጫና የተሳኩ ልምዶችን ለዓለም ማሳየትን ያለመ ነው።

መድረኩ ላይ አዲስ አበባ በቀዳማይ ልጅነት ልማት ዘርፍ ያከናወነችው ተግባራት በተሞክሮነት እንደሚቀርቡ ታውቋል።

የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ከበደ ወርቁ እንደገለጹት፣ አዲስ አበባ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ማዕከሉን በማቋቋም ረገድ ሰፊ ተግባራትን አከናውናለች።

በተለይም በእናቶችና ሕፃናት ጤና ጥበቃ፣ በቅድመ-አንደኛ ደረጃ ትምህርት ማስፋፋት፣ በህፃናት ማቆያ አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራት፣ እንዲሁም ለህፃናት ምቹ የመጫወቻ ስፍራዎችን በመገንባት ረገድ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል።

በዚህ የመጀመሪያው አህጉራዊ ጉባኤ ላይ ከአፍሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ከኢስያ እና ከሌሎች አህጉራት የሚመጡ ከ350 በላይ ባለሙያዎች እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ይሳተፋሉ።

እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚው ገለፃ ፣ ይህ ጉባኤ በቀጣይ አድማሱን በማስፋት በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ይሆናል።

በአሰግድ ኪዳነማርየም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review