የ1447ኛው የሐጅ ጉዞ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

You are currently viewing የ1447ኛው የሐጅ ጉዞ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

AMN-ግንቦት 01/2018 ዓ.ም

የ1447ኛው የሐጅ ጉዞ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅጥር ግቢ ተካሂዷል።

የሐጅ መርሃ-ግብሩን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሐጅ ኢብራሄም ቱፋ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግቢ ተገኝተው በይፋ አስጀምረዋል።

ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጅ ኢብራሄም ቱፋ መርሃ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት፤ የ1447ኛው የመጀመሪያ ዙር የሐጅ ጉዞ በይፋ መጀመሩን ገልጸዋል።

የሐጂ ጉዞ ለሚያደርጉ የእምነቱ ተከታዮችም የመልካም ጉዞ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

መንግሥት የሐጅ ጉዞን የተሳለጠ ለማድረግ ከምዝገባና ክፍያ ስርዓት ጀምሮ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም ለሐጂ ተጓዦች ለሚያደርገው የተሳለጠ አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ኃላፊ ለማ ያደቻ፤ አየር መንገዱ የሐጅ ተጓዦችን በማመላለስ ረገድ የረዥም ጊዜ ታሪክ እንዳለው ገልጸዋል።

ዘንድሮም ይህን የረዥም ዘመን አገልግሎት በማለቅ ጉዞው የተመቸና የተሳለጠ ለማድረግ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

የዚህ ዓመት የሀጅ በረራ ዛሬ ምሽት የሚጀምር ስለመሆኑም በበረራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ተመላክቷል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review