ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኦሲስ አጠቃላይ ሆስፒታልን መርቀዉ ሥራ አስጀመሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኦሲስ አጠቃላይ ሆስፒታልን መርቀዉ ሥራ አስጀመሩ

AMN ግንቦት 2/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ የኦሲስ አጠቃላይ ሆስፒታልን መርቀን ሥራ አስጀምረናል ብለዋል፡፡

የኦሲስ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሀገራችን ጥራት ያለው ሕክምና ለማቅረብ አማራጭ ይዞ የመጣ ማዕከል ነው።

አቅም ያላቸው ውጭ ሀገር ድረስ በመሄድ መታከም ይችላሉ፤ አቅም የሌላቸው ዜጎቻችን ደግም በሃገር ውስጥ ታክመው እንዲድኑ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ ትብብር ዘመኑን የዋጁ ሆስፒታሎች እንዲገነቡ እያደረግን ነው ብለዋል፡፡

ተቋሙ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ለጀመርነው ጉዞ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ስኬታማ እንዲሆን እመኛለሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review