የፈረንሳይ – አፍሪካ ትብብር

You are currently viewing የፈረንሳይ – አፍሪካ ትብብር

AMN – ግንቦት 5/2018 ዓ.ም

የፈረንሳይ እና አፍሪካ ግንኙነት በታሪክ፣ በመልክአ-ምድራዊ ቅርበት የተሳሰረ እና ዘርፈ-ብዙ መልክ ያለው ነው።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ፈረንሳይ በአፍሪካ ያላትን ቀዳሚ የሆነ የኢኮኖሚ አጋርነት አጠናክራ የቀጠለች ሲሆን ፤ እ.አ.አ በ2024 ከ65 ቢሊዮን ዩሮ በላይ የሁለትዮሽ ንግድ ልውውጥ ማከናወኗን መረጃዎች ያሳያሉ።

በአሁኑ ወቅት በአህጉሪቱ የሚንቀሳቀሱ ከ4 ሺህ 400 በላይ የፈረንሳይ ኩባንያዎች ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ አፍሪካውያን የስራ ዕድል ፈጥረዋል። ይህ ዘርፈ-ብዙ አጋርነት በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ ይበልጥ ተጠናክሯል።

በዚህ ጉባዔ ላይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ይፋ እንዳደረጉት፤ በአህጉሪቱ የ23 ቢሊዮን ዩሮ ግዙፍ ኢንቨስትመንት ይተገበራል። 14 ቢሊዮን ዩሮ ከፈረንሳይ የመንግሥት እና የግል ተቋማት የሚመደብ ሲሆን ቀሪው 9 ቢሊዮን ዩሮ ደግሞ ከአፍሪካውያን ባለሀብቶች የሚመጣ ነው። ይህም በዋናነት በኃይል ሽግግር፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ፣ በባህር ኢኮኖሚ እና በግብርና ላይ ያተኩራል፡፡

በአጠቃላይ 250 ሺህ ቀጥተኛ የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ግንኙነት ለመፍጠር እየሠሩ ይገኛሉ።

በቅኝ ግዛት ወቅት የተዘረፉ ቅርሶችን የመመለስ ሂደት እና ሽብርተኝነትን ከመቀነስ አንፃር የሚወሰዱ እርምጃዎችም ተጨማሪ የአዲሱ ፖሊሲያቸው አካል ነው።

በትዝታ መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review