የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት ለዓለም ሰላምና ብልጽግና ወሳኝ ነው- ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ

You are currently viewing የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት ለዓለም ሰላምና ብልጽግና ወሳኝ ነው- ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ

AMN- ግንቦት 6/2018 ዓ.ም

በቻይና እና በአሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት በዓለም ላይ “በጣም አስፈላጊው የሁለትዮሽ ግንኙነት” ነው ሲሉ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ገልጸዋል።

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የ1.7 ቢሊየን ዜጎቻቸውን ደህንነት ብቻ ሳይሆን፣ ከ8 ቢሊየን በላይ የሚሆነውን የዓለም ሕዝብ ጥቅም የሚነካ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ አያይዘውም፣ አሜሪካ ከፉክክር ይልቅ ትብብርን እንድታጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንት ሺ ለሁለቱ ሀገራት የጋራ ልማትና መጻኢ እድል የመልካም ምኞት መግለጫ በማቅረብ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ እንደ ኢሎን ማስክ እና ቲም ኩክ ያሉ ታዋቂ ቢሊየነሮች እንዲሁም ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለሁለቱ ሀገራት ብሩህ ተስፋ ጽዋቸውን በማንሳት ንግግራቸውን በደስታ ማጠቃለላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review