AMN- ግንቦት 5/2018 ዓ.ም
በተስተካካይ የሊግ መርሐግብሩ በኢትሃድ ክሪስታል ፓላስን ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ 3ለ0 አሸነፈ።
አንቷን ሴሜንዮ ፣ ኦማር ማርሙሽ እና ሳቪንሆ ያስቆጠሯቸው ግቦች ሲቲን በዋንጫ ፉክክሩ አቆይተዋል።

በጨዋታው ፔፕ ጋርዲዮላ በመጀመሪያ አሰላለፉ የስድስት ተጫዋቾች ለውጥ ማድረጉ ፣ ሴሜንዮ እስኪያስቆጥር የነበረው የቡድኑ እንቅስቃሴ አመርቂ አለመሆኑ ፣ በኢትሃድ የነበረው ድጋፍ መቀዛቀዙ ሲቲ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫው ላይ ተስፋ የቆረጠ አስመስሎት ነበር።
ነገር ግን ሲቲ ጨዋታውን አሸንፎ አሁንም በቀሪ ጨዋታዎች በፉክክሩ መቆየት እንደሚችል አሳይቷል።

ከሊጉ መሪ አርሰናል እኩል 36 ጨዋታ ያደረገው ማንችስተር ሲቲ ነጥቡን ወደ 77 ከፍ አድርጓል። ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነትንም ወደ ሁለት ነጥብ አጥብቧል።
የፊታችን ቅዳሜ በኤፍ ኤ ካፕ ፍፃሜ ቼልሲን የሚፋለመው ሲቲ ፣ በቀሪ ሁለት የሊግ ጨዋታዎቹ ቦርንማውዝ እና አስቶንቪላን ይገጥማል።
በሸዋንግዛው ግርማ