የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ግንቦት 09/2018 ዓ.ም

የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

በ93.9 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ዘመናዊው የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ትላንት ተመርቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት ፣ የፓርኩ ግንባታ እንደ ከዚህ ቀደሙ መሬትን ብቻ ወስዶ አርሶ አደሩን ያገለለና የገፋ ሳይሆን አርሶ አደሩን የልማቱ ዋና ተባባሪ ያደረገ አካታች ፖሊሲን የተከተለ ነው።

ከንቲባዋ የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ባብራሩበት ገለጻቸው ፣ ከስፍራው ከተነሱት አርሶ አደሮች መካከል ግማሽ ያህሉ በልዩ ሁኔታ በተደራጀው የግብርና ልቀት ማዕከል ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ ተደርጓል ብለዋል።

የተቀሩት አርሶ አደሮች በከተማዋ እየተገነቡ ባሉ የቤት ፕሮጀክቶች ውስጥ የራሳቸው ሼር እንዲኖራቸው መደረጉን ነው የገለጹት።

ከአካባቢው የተነሱት ወገኖች በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ በተገነቡት አነስተኛ ሱቆች የመሸጫ ሱቅ ባለቤት እንዲሆኑና የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ ከተያያዥ የሥራ ዕድሎች ጋር እንዲተሳሰሩ መመቻቸቱንም ከንቲባዋ ተናግረዋል።

ከንቲባ አዳነች ፣ የአዲስ አበባ ለውጥ ማንንም የሚያፈናቅል ሳይሆን ከከተማዋ ዕድገት ጋር አብሮ የነዋሪውና የአርሶ አደሩ ሕይወትና አኗኗር እንዲዘምንና እንዲለወጥ የሚያደርግ መሆኑን አስገንዝበዋል።

እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ የነበረውን መሬት በፈቃደኝነት ለለቀቁ አርሶ አደሮች ከንቲባ አዳነች አቤቤ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።

በታደሠ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review