AMN- ግንቦት 10/ 2018 ዓ.ም
“የባህል ልማት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት!” በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ የባህልና ቋንቋ ሳምንት ተጠናቀቀ፡፡
በመርሃ ግብሩ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ፤ የበለፀገችና ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለንን የባህል እሴቶቻችን በተገቢው መንገድ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ሀገር አቀፉ የባህልና ቋንቋ ሳምንት የኢትዮጵያን ውበት ለዓለም ያስተዋወቀ ነበር ብለዋል።
በቀጣይ በባህል ልማት ላይ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በመግለጽ የባህል እሴቶችን የበለጠ በማልማት ለህዝቦች አብሮነትና ለገፅታ ግንባታ መጠቀም ይገባልም ነው ያሉት፡፡

በሀገር አቀፉ የባህልና ቋንቋ ሳምንት ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉ ሲሆን የየራሳቸውን ባህላዊ እሴቶች አስተዋውቀዋል።
በመድረኩ ለተሳተፉ እና የሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ባህላዊ ሀብቶች፣ ትውፊታዊ እሴቶች እና መገለጫዎች እንዲተዋወቁ ላደረጉም የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
በመሀመድኑር ዓሊ