AMN ግንቦት 13/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ 171 ሺህ 690 ተማሪዎች የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናዎችን እንደሚወስዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
ቢሮው የ2018 የትምህርት ዘመን ከተማ አቀፍ የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና እና የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት የሚሰጥበትን ጊዜ ይፋ አድርጓል፡፡
ከተማ አቀፍ የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ሰኔ 8 ፣ 9 እና 10/2018 ዓ.ም እንዲሁም የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ፈተና ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ቢሮው ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ሚዲያ በላከዉ መረጃ አስታውቋል፡፡

ከሰኔ 8 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሚሰጠው በዚህ ከተማ አቀፍ ፈተና 84 ሺህ 882 የ6ኛ ከፍል ተማሪዎች በ199 የመፈተኛ ጣቢያዎች እንዲሁም 86 ሺህ 808 የ8ኛ ከፍል ተማሪዎች በ201 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን ተገልጿል፡፡