በወንጀል መከላከል ረገድ ያሉ ስኬቶችን በምርጫ ወቅትም አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ

You are currently viewing በወንጀል መከላከል ረገድ ያሉ ስኬቶችን በምርጫ ወቅትም አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ

AMN – ግንቦት 17/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአጋዥ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በወንጀል መከላከል ረገድ ያሉ ስኬቶችን በምርጫው ወቅትም አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገለጸ።

ቢሮው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ወንጀልን በመከላከል ረገድ ከተለያዩ የጸጥታ ኃይሎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

አጋዥ የጸጥታ ኃይሎች የተቋማት እና የአካባቢያቸውን ደኅንነት ከመጠበቅ ባሻገር ወንጀልን ቀድሞ በመከላከል ረገድ ሚናቸውን እየተወጡ መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ፤ ከአጋዥ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በወንጀል መከላከል ረገድ ያሉ ስኬቶችን በምርጫውም ወቅት አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል።

ኃላፊዋ፤ አጋዥ የጸጥታ ኃይሎች የተቋማት እና የአካባቢን ደህንነት መጠበቅ ለከተማዋ ሰላም መጽናት ከፍተኛ አበርክቶ እንዳላቸውም ተናግረዋል።

ለግል ጥበቃ ኤጀንሲ ባለቤቶች እና የጥበቃ ሰራተኞች፣ ለማህበር ቤት ሰብሳቢዎች፣ ለጋራ መኖሪያ ቤት አመራሮች እንዲሁም ለሞተር ማህበር አመራሮች እና ሞተረኞች፣ ለሰላም እና ጸጥታ ስራ ስኬት ያላቸውን ሚና በተመለከተ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review