AMN-ግንቦት 23/2018 ዓ.ም

ነገ በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ድምጻቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ነዋሪዎቹ ለኤ ኤም ኤን በሰጡት አስተያየት፤ ለኢትዮጵያ ልማት ይበጃል የምንለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ዕለቱን በጉጉት እየጠበቅን ነው ብለዋል፡፡

የመራጭነት ካርድ የወሰዱ ዜጎች በምርጫው በንቃት በመሳተፍ ሕገ መንግሥቱ የሰጣቸውን መብት በአግባቡ ሊጠቀሙ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የአዲስ አበባ ከተማ የአቃቂ ቃሊቲ የምርጫ ክልል 26 እና 27 ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ለድምፅ መስጫው ዕለት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ኤ ኤም ኤን ባደረገው ቅኝት ተመልክቷል።
በመሀመድኑር ዓሊ