በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡት የገበያ ማዕከላት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋትና ምርትን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያበረከቱ ይገኛሉ – ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ

AMN-ሰኔ 8/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገበያ ማረጋጋት፣ የሕገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር እና የኢትዮጵያ ታምርት ግብረ-ኃይል ያለፉት ወራት አፈፃፀም እና የቀጣይ የክረምት ወራት የሥራ አካሄድን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ ባለፉት ወራት ከምርት አቅርቦት፣ ከግብይት ሰንሰለት፣ ከዋጋ ቁጥጥር እና ከተያያዙ የግብይት ሂደቶች አንጻር የተከናወኑ ተግባራትን የሚያሳይ ዝርዝር የሥራ ሪፖርት ቀርቧል።

በቀረበው ሪፖርት ላይ በተለይም የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እና ከዓለም አቀፍ ገበያ አንጻር የሀገር ውስጥ ገበያን ለመቆጣጠር በግብረ-ኃይሉ በርካታ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸው ተመልክቷል።

በዚህም በከተማዋ ከተገነቡት ሰባቱም ሁለገብ የገበያ ማዕከላት በተጨማሪ፣ በ256 የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ከግብርና እስከ ኢንዱስትሪ ምርቶች በጥራትና በስፋት ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለ በሪፖርቱ ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፤ የገበያ ማዕከላቱ በከተማ አስተዳደሩ በስፋት የለሙት ገበያን በዘላቂነት ለማረጋጋትና የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማስተካከል ስለመሆኑ አንስተዋል።

የምርት አቅርቦትን ማሻሻልና ተደራሽነትን ማረጋገጥ ላይ ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ምክትል ከንቲባው፤ የግብይት ስርዓቱን ጤናማ ለማድረግ ሕገ-ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ሕጋዊ መስመር ለማምጣት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በቀጣይ የክረምት ወራትም የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን ይበልጥ አጠናክሮ በማስቀጠል፣ በአቅርቦትና በስርጭት ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት እንደሚገባ በመድረኩ ላይ ተመላክቷል።

በትባረክ ኢሳያስ

See less

Muna Arada

 ·

ገበያን ማረጋጋት የሚቻለው በዋጋ ቁጥጥር ብቻ ሳይሆን በቂ አቅርቦት በማረጋገጥ ነው። በአዲስ አበባ የተፈጠሩት ሰባት ሁለገብ የገበያ ማዕከላትና 256 የሳምንት መጨረሻ ገበያዎች ምርቶች በብዛትና በተደራሽነት ለሕዝብ እንዲቀርቡ ያደረጉት አስተዋፅዖ ከፍተኛ ነው። ይህ አካሄድ በቀጣይም በቴክኖሎጂ፣ በዘመናዊ ሎጂስቲክስ እና በግብይት ቁጥጥር ተደግፎ ከቀጠለ የከተማዋን የኢኮኖሚ መረጋጋት ይበልጥ ያጠናክራል።

Reply

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review