AMN- ሰኔ 18/2018 ዓ.ም
8ኛው ዓለም አቀፍ አግሮ ፉድ እና ፕላስትፕሪንትፓክ ኢትዮጵያ እንዲሁም 2ኛው የኢትዮጵያ የምግብ እና ኢቲዮፒካ የቡና ንግድ ትርዒት በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል።
የሀገር ውስጥ እና የውጭ አምራቾችን፣ ነጋዴዎችን እና ባለሀብቶችን በአንድ ጣሪያ ስር ያገናኘው ይህ የንግድ ትርኢት በዛሬው እለት በአዲስ አለማቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በይፋ ተከፍቷል።

ንግድ ትርኢቱ የግብርና ኢንዱስትሪ ምርቶችን፣ የምግብ አዘገጃጀትና የምግብ ኢንዱስትሪን፣ የፕላስቲክ፣ ህትመትና ማሸጊያ ቴክኖሎጂዎችን እንዲሁም የኢትዮጵያን ምርጥ ቡና በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ ሰፊ የንግድ መድረክ ነው።
የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን በዚህ ዓለም አቀፍ መድረክ በመሳተፍ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብቶች እንዲሁም የቱሪዝም ኢንቨስትመንት አማራጮችን ለውጪና ለሀገር ውስጥ ጎብኚዎች እንዲሁም ለመድረኩ ተሳታፊዎች እያስተዋወቀ እንደሚገኝ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።