ታላላቅ ፕሮጀክቶች ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁ በቴክኖሎጂ የታገዘ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

AMN -ሰኔ 30/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ እየተገነቡ ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁ በቴክኖሎጂ የታገዘ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት፤ በመላው ኢትዮጵያ ያለውን የመንገድ ሥራ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማሟላት ቢያንስ ሁለት ትሪሊየን ብር በጀት ይፈልጋል ብለዋል፡፡

በዚህም ሁሉንም በጀት ለመንገድ ብቻ ማዋል ስለማይቻል ፕሮጀክቶችን በቅደም ተከተልና በአዋጭነት መለየት ይገባል ነው ያሉት።

በሌላ በኩል በአንዳንድ አካባቢዎች የቀበሌና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ነጋዴዎች ባላቸው ትስስር ከፕሮጀክቱ ጠቀሜታ በላይ በካሳ ለመጠቃቀም በሚያደርጉት ጥረት ፕሮጀክቶች እንደሚጓተቱ አብራርተዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየተገነቡ ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁ በቴክኖሎጂ የታገዘ ጥብቅ የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓት እየተተገበረ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በዚህም በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ መሻሻል መታየቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review