አዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ማዕከል ብቻ ሳትሆን የዓለም የኢኮኖሚ መዳረሻ ናት

You are currently viewing አዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ማዕከል ብቻ ሳትሆን የዓለም የኢኮኖሚ መዳረሻ ናት

AMN- ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ማዕከል ብቻ ሳትሆን የዓለም የኢኮኖሚ መዳረሻ መሆኗን የ49ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ተሳታፊዎች ተናገሩ፡፡

የዓለም የፖለቲካ መልህቅ፣ የአፍሪካም ከተሞች ፊታዉራሪዋ አዲስ አበባ ከተማ 49ኛዉን የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ጉባኤ እያስተናገደች ትገኛለች።

ለዓመታት አዲስ አበባን የረገጡና በአዲስ አበባ ከተማ መሰረተ ልማት እጦት አብዝተው የተማረሩ ብዙዎች ነበሩ።

ዛሬ ግን ታሪክ ተቀይሯል፤ አዲስ አበባ ከተማ የኢትዮጵያዊያን ኩራት፣ የአፍሪካዊያን መናገሻ እና የዓለም ቱሪስቶችም መዳረሻ ሆናለች።

ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉት ከአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አናስ ቺቸል እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት የጃፓን አምባሳደር ኖቦሩ ሲኪቢጂ ለአዲስ አበባ ለውጥ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

ለዓመታት አዲስ አበባ የተመላለሱ እና ዛሬ ደግሞ ለ49ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ከተማ የከተሙ የጉባኤው ተሳታፊዎች፤ የመዲናዋ መሰረተ ልማት ስሉጥነት እና ቅንጅት የህዝቡ እንግዳ ተቀባይት እንዲሁም የመሰረተ ልማቱን ፍጥነትና ጥራት አድንቀዋል።

ይህም አዲስ አበባ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል እና የዓለም አይኖች የትኩረት ማዕከል እንድትሆን እንዳስቻላት ምስክርነት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ የዓለም የፖለቲካ ምህዋር ብቻ ሳትሆን፣ የዓለም የኢኮኖሚ ማዕከል ለመሆን እየሰራች ነው የሚሉት ተሳታፊዎቹ፣ በኢትዮጵያ ከተሞች የሚታዩ ተጨባጭ ውጤቶች ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ናቸው ብለዋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች በከተማ ማዘመን እና በመሰረተ ልማት ዘርፍ ላይ የተገኙ ውጤታማ ተግባራት በአፍሪካዊያን ዘንድ ሊቀመሩ እንደሚገባም ተናግረዋል።

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review