ጀግኖች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የነገሱባት ኮፐንሃገን

You are currently viewing ጀግኖች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የነገሱባት ኮፐንሃገን

AMN- መስከረም 9/2019 ዓ.ም

በአንድ ሳምንት ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያስመዘገበችው አትሌት ልቅና አምባው የብዙዎችን ቀልብ ስባለች።

ዛሬ የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና በዴንማርክ ኮፐንሃገን በድምቀት ተጀምሯል።

በውድድሩ የመጀመሪያ ቀንም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ የሀገራቸውን ስም ከፍ አድርገዋል።

በተለይም አትሌት ልቅና አምባው አስደናቂ ብቃቷን በማሳየት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለኢትዮጵያ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አስገኝታለች።

ባሳለፍነው ሳምንት በቡዳፔስት በተካሄደው የአልቲሜት ሻምፒዮና ወርቅ ሜዳሊያ ያሸነፈችው ልቅና ዛሬም በኮፐንሃገን በሴቶች 5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ወርቅ በማምጣት አስደናቂ ድል አስመዝግባለች።

በሴቶች 5 ኪ.ሜ ውድድር የተሳተፈችው አትሌት አለሺኝ ባወቀም ውድድሩን 5ኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቋን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በ1 ማይል ውድድር ደግሞ ጀግናዋ አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ በጠንካራ ፉክክር የብር ሜዳሊያ አሸንፋለች።

በወንዶች 5 ኪ.ሜ ውድድር አትሌት አዲሱ ይሁኔ 6ኛ ደረጃን፣ አትሌት መዝገቡ ስሜ ደግሞ 7ኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩን አጠናቀዋል።

በተጨማሪም በሴቶችና በወንዶች 5 ኪ.ሜ ውድድር በተመዘገቡ ውጤቶች መሠረት ኢትዮጵያ በቡድን ውጤት የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆናለች።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review