የቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በ”አንድ ጀምበር” የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተሳትፎ እያደረጉ ነው

You are currently viewing የቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በ”አንድ ጀምበር” የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተሳትፎ እያደረጉ ነው

AMN – ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም

በመላ ሀገሪቱ 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር ለመትከል በተያዘው ታሪካዊ ዕቅድ መሰረት፤ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በተለይም የቦሌ ክፍለ ከተማ ማህበረሰብ ከማለዳው ጀምሮ በነቂስ በመውጣት በቦሌ ቡልቡላ አሻራቸውን እያሳረፉ ይገኛሉ።

«ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ሀገራዊ መርሐ ግብር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ለመትከል ካቀደው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ችግኝ ውስጥ ክፍለ ከተማው የራሱን ከፍተኛ ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡

በመርሐ ግብሩ የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኮራን ጨምሮ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት፣ ወጣቶች፣ አዛውንቶች እና ህፃናት በጋራ በመሆን ለምግብነት እና ለውበት የሚያገለግሉ፣ እንዲሁም የደን ሽፋንን የሚያሳድጉ ችግኞችን በስፋት እየተከሉ ነው፡፡

እንደ ሀገር ባሳለፍነው ዓመት በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ትልቅ ስኬት የተመዘገበ ሲሆን፤ የዘንድሮውን የ800 ሚሊዮን ዕቅድ ለማሳካትም ህዝቡ በከፍተኛ መነሳሳት ላይ ይገኛል።

በትዝታ መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review