ፌዴራል ፖሊስ ሰላምና ጸጥታ ከማስከበር ጎን ለጎን የሀገሪቱን ልማት ለማፋጠን የራሱን አሻራ እያበረከተ ነው – ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል

You are currently viewing ፌዴራል ፖሊስ ሰላምና ጸጥታ ከማስከበር ጎን ለጎን የሀገሪቱን ልማት ለማፋጠን የራሱን አሻራ እያበረከተ ነው – ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል

AMN – ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የሀገሪቱን ሰላምና ጸጥታ ከማስከበር ጎን ለጎን የሀገሪቱን ልማት ለማፋጠን የራሱን አሻራ እያበረከተ እንደሚገኝ የፌዴራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ።

ኮሚሽነር ጀነራሉ ይህንን የገለጹት “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሀሳብ በመላ ሀገሪቱ በተካሄደው በአንድ ጀምበር የ800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ችግኝ በተከሉበት ወቅት ነው።

በመርሃ ግብሩ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የፖሊስ አመራሮችና አባላት ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመቀናጀት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞችን መትከላቸውን ጠቅላይ አዛዡ አስታውሰዋል።

ኮሚሽነር ጀነራሉ ችግኝ መትከል ብቻውን በቂ አለመሆኑን ጠቅሰው፣ የተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ አስፈላጊው እንክብካቤና ክትትል ሊደረግላቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተለይም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ተማሪዎች በግቢው ውስጥ በሚኖራቸው የቆይታ ጊዜ የተተከሉትን ችግኞች በቅርበት እየተከታተሉ በመንከባከብ እንዲያጸድቁ ሊያደርጉ እንደሚገባ መግለፃቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review