ከተማችንን በአብሮነት እናልብስ – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እየተካሄደ ያለው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የማበረታቻ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፤ እንበርታ!! ከተማችንን በአብሮነት እናልብስ! ብለዋል፡፡

በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር፣ ከተማችን አዲስ አበባ 1 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅዳ ማልዳ የተነሳች መሆኑን አንስተዋል፡፡

የከተማችን ነዋሪ “ተስፋን መትከል የሁላችን ዋነኛ ሀላፊነት ነው!” በሚል ስሜት ባሳየው ጠንካራ ርብርብ እስካሁን ከዕቅዳችን በላይ 1.4 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ባለቤትነቱን በተግባር አሳይቷል ብለዋል።

አሁንም ቢሆን መላው የከተማችን ነዋሪዎች ይህንን የጀመርነውን እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ ርብርባችንን በማስቀጠል፤ የከተማችንን ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪካዊ አሻራ ማኖራችንን ጠንክረን እንቀጥል፣ እንበርታ ሲሉ ከንቲባ አዳነች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review