AMN- ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በሁለተኛ ዙር የሰለጠኑ 864 የፖሊስ መኮንኖችን መርቀናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ ተመራቂ የፖሊስ መኮንኖች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በሁለተኛ ዙር የሰለጠኑ 864 የፖሊስ መኮንኖችን መርቀናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ተመራቂዎች በቆይታችሁ ያገኛችሁት እውቀት ለላቀ ፖሊሳዊ ስብዕና የሚያበቃችሁ እንደመሆኑ ወደ ስራ ስትሰማሩም ያለአድልዎና ልዩነት በታማኝነት፣ በጀግንነት፣ በሰብዓዊነትና በክብር፣ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እንደምታገለግሉ ሙሉ እምነት አለኝ ሲሉም ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡