ምክረ ሀሳቦች እና አጀንዳዎችን በአንድ ወጥ ሰነድ የማጠናቀር ሥራ ተከናውኗል-ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

You are currently viewing ምክረ ሀሳቦች እና አጀንዳዎችን በአንድ ወጥ ሰነድ የማጠናቀር ሥራ ተከናውኗል-ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

AMN – ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በስምንቱም ቡድኖች የተሰበሰቡትን ምክረ ሀሳቦች እና አጀንዳዎች በአንድ ወጥ ሰነድ የማጠናቀር ሥራ መከናወኑን ገለጸ።

የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገብረሥላሴ በሰጡት መግለጫ፣ ከስምንቱም ቡድኖች የተወጣጡ 120 አጠናቃሪ ተሳታፊዎች ላለፉት ቀናት ጥንቃቄ በሚፈልገው በዚህ ሥራ ላይ ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

ሰነዱ ዝግጁ ከሆነ በኋላ ለሁሉም ቡድኖች እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን፣ ቡድኖቹም በሰነዱ ላይ ተጨማሪ ግብዓቶችንና አስተያየቶችን ሲሰጡ መዋላቸውን ጠቅሰዋል።

አጠናቃሪ ቡድኑ የተሰጡትን የመጨረሻ ግብዓቶች በማካተት ሰነዱን ሙሉ በሙሉ ዛሬ እንደሚያጠናቅቅ የገለጹት ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ፣ ግብዓቶችን በማካተት ያጠናቀቁትን ሰነድ በነገው ዕለት ለ4 ሺህ የጉባዔው ተሳታፊዎች እንደሚቀርብ አስታውቀዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገብረሥላሴ ፣ የምክክር ሂደቱ አስፈላጊ በሆነው የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የጠቆሙ ሲሆን፣ ህዝቡም ያልተረጋገጡና የተዛቡ መረጃዎችን ከመስማት ተቆጥቦ ትክክለኛ የሆኑ ሚዲያዎችንና የኮሚሽኑን ኦፊሴላዊ መግለጫዎች ብቻ እንዲከታተል ጥሪ አቅርበዋል።

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review