በመዲናዋ የተተገበሩ የኮሪደር እና ወንዝ ዳርቻ ልማቶች የነዋሪዎችን ጤና እና የአኗኗር ዘይቤ የሚያዘምኑ ናቸው

AMN- ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ እየተተገበሩ ያሉ የኮሪደር እና ወንዝ ዳርቻ ልማቶች ከገጽታ ግንባታ ባለፈ የነዋሪዎችን ጤና እና የአኗኗር ዘይቤ የሚያዘምኑ መሆናቸውን የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተሳታፊዎች ተናገሩ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ጎስቋላ ገጾቿን አስውበው ወንዞቿንም ከተፈጥሮ ጋር አስታርቀው የዓለም የስበት ማዕከል አድርገዋታል፡፡

የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተሳታፊዎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለማስፋፋት ዓላማ ያደረገ የጋራ የእግር ጉዞ አካሂደዋል፡፡

ከ56 አገራት የመጡ የጤና መሪዎች እና ባለሙያዎች የተሳተፉበት የእግር ጉዞው ከአድዋ ድል መታሰቢያ ተነስቶ በከተማዋ የእግረኛ መንገድ በመከተል መስቀል አደባባይ ላይ የተጠናቀቀ ነው።

የእግር ጉዞው “ንግግርን ወደ ተግባር” በሚል መሪ ሐሳብ የ3.5 ኪሎ የሸፈነ ሲሆን፣ የመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ እየተተገበሩ ያሉ የኮሪደር እና ወንዝ ዳርቻ ልማቶች ከገጽታ ግንባታ ባለፈ ለነዋሪዎች ጤና እና የአኗኗር ዘይቤ የሚያዘምኑ መሆናቸውን ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል፡፡

ኮሪያዊቷ ካይ ሚን ኪን እና ኢንዶኔዥያዊዉ አይረማን ትሪታማ እንዲሁም ጃፓናዊቷ ኤኒቢስኪ የመዲናዋ ዝና በተለያዩ አማራጮች ከመከታተል ባለፈ በአካል ተግኝተን ስንመለከት ግርምትን ፈጥሮብናል ብለዋል፡፡

የከተማዋን ውበት፣ ጽዳት እንዲሁም የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶችን ያደነቁት ተሳታፊዎቹ ይህም ለነዋሪዎች የኑሮ ዘይቤ ለማሻሻል እና ጤና ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ ሁለንተናዊ ለዉጥ መደመማቸዉን የገለጹት ደግሞ ከተማዋን በተዳጋጋሚ የጎበኙ ሴራዊሊዮናዊዉ ቲቪን ካግባ እና ጊኒያዊዉ ዶክተር ሻማሪ ኪፔላ ናቸው፡፡

በከተማዋ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች መዲናዋ ለጤና ዘርፉ ተመራጭ ጤናማ ትዉልድም የሚገነባባት ትሆን ዘንድ እድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡

ከተማዋ ፕሮጀክቶችን በጥራት እና በፍጥነት የማጠናቀቅ ተግባር ለሌሎች ሀገራትም በተሞክሮ መልክ የሚቀመር ነዉ ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ላይ ሆነዉ ወዳጅ ዘመድ እና ጓደኞቻቸዉ ከመላዉ ዓለም አዲስ አበባን ይጎበኙ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በከተማዋ ፕሮጀክቶችን በጥራት እና በፍጥነት የማጠናቀቅ ተግባር ለሌሎች ሀገራትም ተሞክሮ የሚሆን ነውም ብለዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review