AMN – ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም

ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተጠቃሚነት የሠራነው ልማት በተጨባጭ አዳዲስ የአኗኗር ባህል እየገነባ ማኅበራዊ መሥተጋብርን ይበልጥ እያጠናከረ ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በውቧ ካዛንችስ የገንባነው ስፖርት ፓርክ ለከተማችን ነዋሪዎች የጤንነት መጠበቂያ ፣ የአካልና አእምሮ ማጎልበቻ ፣ የሕጻናት መቦረቂያ፣ የብሔራዊ ጀግኖች አትሌቶቻችን ውለታ መታሰቢያ አካታች ልማት በመሆኑ ለሁሉም የማሕበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡