ኪነ-ጥበብ ወጣቶች ሀገር ወዳድ እንዲሆኑና የወል ትርክት እንዲኖራቸው ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው

You are currently viewing ኪነ-ጥበብ ወጣቶች ሀገር ወዳድ እንዲሆኑና የወል ትርክት እንዲኖራቸው ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው

AMN – ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም

ኪነ-ጥበብ ወጣቶች ሀገር ወዳድ እንዲሆኑ፣ ሀገራቸውን እንዲያለሙ እና ስለሀገራቸው ጠንካራ የወል ትርክት እንዲኖራቸው ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ባህል እና ኪነ-ጥበብ ቢሮ “ጽኑ ሀገር በኪነ-ጥበብ” በሚል መሪ ሀሳብ አብርሆት የጥበብ ማዕድ መድረክ በቀበና ፓርክ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ ወጣት እና ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን ጨምሮ በየክፍለ ከተማው የሚገኙ የኪነ-ጥበብ ማዕከላት የተለያዩ ኪናዊ ሥራዎቻቸውን ለተመልካች አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ባህል እና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሉባባ ጀማል በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ ቢሮው በየጊዜው መሰል የኪነ-ጥበብ መድረኮችን ማዘጋጀቱ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያገናኝ የአብሮነት ድልድይ ፈጥሯል።

መድረኩ ወጣቶች የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ እና በመዲናዋ የተከናወኑ ታላላቅ የልማት ሥራዎችን እንዲያውቁ ሰፊ ዕድል የፈጠረ መሆኑ ተመላክቷል።

በደሳለኝ ሙሐመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review