ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች

You are currently viewing ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች

AMN-ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ጥያቄዋን ያቀረበችበት ሰነድ (Bid Document) ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ማስገባቷን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል።

ፌዴሬሽኑ ከኢፌዴሪ መንግሥት ጋር በጋራ አስፈላጊ ዶክመንቶችን ያካተተ ሰነድ (BID HAND BOOK) ለካፍ አስገብቷል።

ኢትዮጵያ ታላቁን አህጉራዊ የእግር ኳስ ድግስ ለአራተኛ ጊዜ በስኬት ለማስተናገድ ብሎም በአፍሪካ እግር ኳስ ያላትን ጉልህ ታሪክ ዳግም ለማደስ መዘጋጀቷን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review