AMN- ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም
የማንችስተር ዩናይትዱ አማካይ ቡርኖ ፈርናንዴዝ የእንግሊዝ እግርኳስ ተጫዋቾች ማኅበር (PFA) የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል።
ፖርቹጋላዊው አማካይ አብረውት በእጩነት የቀረቡት ዴክላን ራይስ ፣ ጋብርኤል ማጋሌሄሽ ፣ ዴቪድ ራያ ፣ ኧርሊንግ ሃላንድ እና ራያን ቸርኪን በነጥብ በልጦ ነው ማሸነፍ የቻለው።
ፈርናንዴዝ 2010 ላይ ዋይን ሩኒ ካሸነፈ በኋላ ይህን ሽልማት ያገኘ የመጀመሪያው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ሆኗል።
የ31 ዓመቱ ተጫዋች በፕሪምየር ሊጉ የ2025/26 የውድድር ዘመን 21 ግብ የሆኑ ኳሶችን አቀብሏል። በዚህም በአንድ የውድድር ዓመት ከፍተኛ ለግብ የሆኑ ኳሶችን ያቀበለ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን ታሪክ ሰርቷል።
ከዚህ ቀደም ቴሪ ኦንሪ እና ኬቨን ደብሩይና በአንድ የውድድር ዓመት 20 ግብ የሆኑ ኳሶችን በማቀበል የታሪኩ ብቸኛ ባለቤት ነበሩ።
በሴቶች የማንችስተር ሲቲዋ አጥቂ በኒ ሾው ተመርጣለች። ጀማይካዊቷ አጥቂ ቡድኗ የሴቶች ሱፐር ሊግ አሸናፊ ሲሆን ትልቅ ሚና ተወጥታለች።
በሸዋንግዛው ግርማ