ለአፍሪካ የጤና ሥርዓት መሻሻል የዓለም ጤና ድርጅት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል- ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም

AMN – ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም

ለአፍሪካ የጤና ሥርዓት መሻሻል የዓለም ጤና ድርጅት ያላሰለሰ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናገሩ።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ መልዕክታቸውን በበይነ መረብ አስተላልፈዋል።

አፍሪካ በሽታዎችን ቀድሞ የመከላከል እና ለችግሮች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ አቅሞችን እየገነባች መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የአፍሪካን ሁለንተናዊ እድገት እውን ለማድረግ በጤና ዘርፍ ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም መድኃኒት የማምረት አቅምን ማሳደግ፣ የጤና ተቋማትን ተደራሽነት ማስፋት እና የባለሙያዎችን አቅም መገንባት ለዚህም ወሳኝ መሆናቸውን ጠቁመው፣ በእነዚህ ተግባራት የአፍሪካን የጤና ዘርፍ ስኬት ማሻሻል እንደሚጠበቅ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በጉባኤው ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የዓለም ጤና ድርጅት አመራሮች ተገኝተዋል።

በተመስገን ይመር

See less

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review