AMN- መስከረም 2/2019 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋር በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ ወቅታዊ ሁነቶች እና አጠቃላይ በቀጣናው የደኅንነት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋር ተወያይተናል ብለዋል።
ከጉባኤው ጎን ለጎን ያደረግነው ውይይት በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ ወቅታዊ ሁነቶች እና አጠቃላይ በቀጣናው የደኅንነት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው ያሉ ሲሆን፣ የውይይትን አስፈላጊነት እና የቀጣናውን መረጋጋት እውን ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መምከራቸውንም ገልጸዋል፡፡