AMN – መስከረም 2/2019 ዓ.ም
18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ በህንድ ኒው ዴልሂ ባራት ማንዳፓም ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል።
ሕንድ ከአውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር ከጥር 1 ቀን 2026 ጀምሮ የብሪክስ ሊቀመንበርነቱን መረከቧ ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚህ በብሪክስ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሕንድ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺጂንፒንግ ፣ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላዲሚር ፑቲን፣ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን እና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳን ጨምሮ በርካታ የዓለም መሪዎችና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጉባዔው ይሳተፋሉ።
የብሪክስ አባል ሃገራት የዓለምን 49.5% ሕዝብ እንዲሁም የዓለም አቀፉን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት 40% እና የዓለም አቀፍ ንግድ 26% ድርሻን ይሸፍናሉ።
ጉባዔው በቆይታው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።
ስብስቡ ኢትዮጵያ፣ ብራዚል፣ ቻይና፣ ግብፅ፣ ሕንድ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ኢራን፣ ሩሲያ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን ያቀፈ ነው።
በወንድማገኝ አሰፋ