በኮሪደር ልማት ታድሳ የዘመናዊነት ጮራ የፈነጠቀባት አዲስ አበባ

You are currently viewing በኮሪደር ልማት ታድሳ የዘመናዊነት ጮራ የፈነጠቀባት አዲስ አበባ

AMN – መስከረም 9/2019 ዓ.ም

የእይታ ቀልብን የሚስብ፣ የከተማዋን ነባር ገጽታ በአዲስ መልክ የቀየረ እና የነዋሪዎችን ኑሮ ያሻሻለ ሰፊ የኮሪደር ልማት ሥራ ባለፉት ጥቂት አመታት በ24/7 የስራ ባሕል ተሰርቶ መዲናዋን በታላቅ ድምቀት እያስዋባት ይገኛል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ እነዚህ የከተማ ማሻሻያ ሥራዎች አዲስ አበባ ከነበረችበት የዕድሜ ጠገብ ገጽታ በመላቀቅ የዘመናዊነት እና የንጽህና መገለጫ መሆኗ ተገልጿል።

ከለውጡ ወዲህ በዋና ከተማዋ የተጀመሩ ስልታዊ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችና የከተማ እድሳት ሥራዎች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያና የሥራ ከባቢን ፈጥረዋል።

በዘመናዊ የምህንድስና ዲዛይን፣ በሰፊ የእግረኛ መንገዶች፣ በብስክሌት መተላለፊያዎች፣ በዘመናዊ የመብራት ሥርዓቶች እና በለመለሙ አረንጓዴ መናፈሻዎች የታነጸው ይህ የኮሪደር ልማት፤ የከተማዋን የንግድና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሯቸዋል።

የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እና የቱሪዝም ፍሰት ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ ዘመናዊ የመንገድ ትስስሮች፣ የከተማ ማዕከላት እና የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች ተገንብተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የውሃ፣ የፍሳሽ እና የዲጂታል መሠረተ ልማት መረቦች ከዕድሳቱ ጋር ተቀናጅተው በመዘርጋታቸው ከተማዋ ማንኛውንም ዘመናዊ አገልግሎት በብቃት ማስተናገድ የሚችለውን አቅም እንዲኖራት አስችለዋታል።

የአዲስ አበባን ሁለገብ ገጽታና የሕዝብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የእነዚህ የኮሪደር ልማቶች ዋንኛ ዓላማ ሲሆን፤ ይህንን ተግባር እውን ለማድረግ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎችና ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

ከተማዋ ነባር ውበቷን ጠብቃ ከዘመኑ ጋር እንድትታደስ በተደረገው ሰፊ ርብርብ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ መድረኮችን በበለጠ ዝግጁነት የምታስተናግድበት ምዕራፍ ተፈጥሯል።

ኢትዮጵያ በታሪክ ጉዞዋ የገነባቻቸውን እሴቶች በልማት ሥራዎች በማቀንቀን ረገድ አዲስ አበባ የፊት መስመር አርአያነቷን እያስመሰከረች ትገኛለች።

የዛሬው ትውልድ በከተማ ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና በሥነ-ምግባር ያከናወናቸው እነዚህ ግዙፍ የኮሪደር ልማቶች የከተማዋን ሁለንተናዊ ብልጽግና አረጋግጠዋል።

አዲስ አበባ አሁን ላይ የተያዙ የከተማ ልማት ዕቅዶችን በታቀደላቸው ጊዜ ውስጥና በታላቅ ጥራት እውን የማድረግ አቅም ላይ መገኘቷ ለአገሪቱ የኢኮኖሚ ከፍታ እና የብልጽግና ጉዞ ትልቅ ማረጋገጫ ሆኗል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review