AMN ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ/ም

ነገ መስቀል አደባባይ በሚደረገው የህዝብ ንቅናቄ መርሃ ግብር ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በመሆኑም ፕሮግሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ፦
ከመገናኛ በባንቢስ ሱፐር ማርኬት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ
ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ጥላሁን አደባባይ ወይም መሾለኪያ ለከባድ ተሽከርካረዎች አጎና ሲኒማ
ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለገሃር መብራት
ከንግድ ባንክ ወደ አዲስ አበባ ስቴዲዩም ቴሌ መ/ቤት
ከፒያሳ በአምባሳደር ቴአትር ወደ መስቀል አደባባይ ሀራምቤ ሆቴል
ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት
ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ለገሃር መብራት
በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎፒምያ ወይም ደንበል አደባባይ ጋር ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
ይህ መረጃ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ በተጠቀሱት አካባቢዎች ለአጭርም ሆነ ለእረጅም ጊዜ ተሽከርከካሪ አቆሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ዋና መምሪያው ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ ገልጿል።