የቢኒያም እና የሐገረሰላም የMMA ፍልሚያ በቢኒያም አሸናፊነት ተጠናቀቀ

You are currently viewing የቢኒያም እና የሐገረሰላም የMMA ፍልሚያ በቢኒያም አሸናፊነት ተጠናቀቀ

AMN መሰከረም 10/ 2019

ኢትዮ ፋይት ናይት (Ethio Fight Night) ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ምሽት የተካሄደው የEFN የውድድር መርሃ ግብር በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል።

በውድድሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ እንደነዚህ ያሉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ውድድሮች ወደ ከተማችን መምጣታቸው የወጣቱን ብርቱ ፍላጎት ከማሟላቱም ባሻገር ስፖርታዊ እንቅስቃሴን የሚያነቃቁ እና የስፖርት ቱሪዝምን በከተማችንም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋገሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ምክትል ኃላፊው ከተማ አስተዳደሩ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ለስፖርቱ በሰጠው ልዩ ትኩረት ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ ትውልድ በስፋት የሚጠቀምባቸው ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በስፋት ተገንብተዋል ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ገልፀዋል።

በዚሁ ውድድር የሚክስድ ማርሻል አርት (MMA)፣ የቦክስ፣ የሙያታይ፣ የማርሻል ሳንዳ እና የኪክ ቦክስ ውድድሮች ተካሂደዋል።

በውድድሩ በዋናነት እና በብዙዎች ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የታዋቂዎቹ ተወዳዳሪዎች የቢኒያም እና የሐገረሰላም የMMA ፍልሚያ በቢኒያም አሸናፊነት መጠናቀቁን የከተማዉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review