AMN-መስከረም 10/2019 ዓ.ም

በኮፐንሃገን በተደረገው የዓለም የግማሽ ማራቶን የጎዳና ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ታደሰ ወርቁ 4ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል።
ታደሰ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 58:35 የሆነ ሰዓት ፈጅቶበታል። ውድድሩን ስውዲናዊው አንድሬስ አልማግርን 58:06 በሆነ ሰዓት አሸንፏል።
ኬንያዊው ኒኮላስ ኪፕኮሪር 2ኛ ፣ ዩጋንዳዊው ጆሽ ቼፕቴጋይ 3ኛ ደረጃ ይዘው ጨርሰዋል።

ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በላይ ጥላሁን 14ኛ ፣ በረከት ነጋ 15ኛ እንዲሁም ባየልኝ ተሻገር ደግሞ 39ኛ ደረጃ መውጣት ችሏል።