ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከእስራኤሉ አቻቸው ጋር ተወያዩ

AMN – ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከእስራኤሉ አቻቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ብንያሚን ነታንያሁ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው(x) ባስተላለፉት መልዕክት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ብንያሚን ነታንያሁ ጋር ያደረጉት የስልክ ውይይት ፍሬያማና ገንቢ እንደነበር ገልጸዋል።

በውይይቱ ወቅት ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያና በእስራኤል የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም በዋና ዋና ቀጣናዊ ሁነቶች ዙሪያ ሰፊ ምክክሮች ማድረጋቸውም ተጠቅሷል።

በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት በጋራ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን የትብብር ቁርጠኝነት በድጋሚ ማረጋገጣቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት አብራርተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review