የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሩዋንዳን አሸነፈ

AMN-መስከረም 27/2019 ዓ.ም

ለ2028ቱ ኦሊምፒክ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሩዋንዳን ከሜዳው ውጪ 1ለ0 አሸንፋል።

በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተከናወነው የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ የሩዋንዳዋ ኡዛዬ ሴንጋ በራሷ ላይ ያስቆጠረችው ግብ ኢትዮጵያን አሸናፊ አድርጓል።

በጨዋታው በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ውድድር ላይ ለመሳተፍ ሩዋንዳ ያቀናው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ልዑክ ስታዲየም በመገኘት ለሴቶች ብሔራዊ ቡድን ድጋፍ ሰጥቷል።

ቀጣዩን ዙር ለመቀላቀል የተሻለ ዕድል የያዙት ሉሲዎቹ የመልሱን ጨዋታ ጥቅምት 3 በኢትዮጵያ ያደርጋሉ።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review