አዲስ አበባ የስፖርት መሠረተ ልማት ማዕከልነቷን እያጠናከረች ነው

You are currently viewing አዲስ አበባ የስፖርት መሠረተ ልማት ማዕከልነቷን እያጠናከረች ነው

AMN- ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም

አዲስ አበባ የስፖርት መሠረተ ልማትን በማስፋፋት ብቁ እና ተወዳዳሪ ስፖርተኞችን ለማፍራት መሰረት እየጣለች ትገኛለች፡፡

ከተማዋ የስፖርት መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት የጤና፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚ ዕድገት ማዕከልነቷንም እያጠናከረች ነው፡፡

በፈጣን እድገት ላይ በምትገኘው አዲስ አበባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት እየተገነቡ የሚገኙት የስፖርት መሠረተ ልማቶች ለከተማዋ በርካታ ጥቅሞችን እያበረከቱ ይገኛል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ እያስፋፋ ያለው የስፖርት መሠረተ ልማት በከተማዋ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባህል እንዲዳብር አድርጓል፡፡ ይህም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ከመከላከል ባለፈ ጤናማ እና አምራች ህብረተሰብ ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽዖ እያበረከተ ይገኛል።

በከተማዋ የስፖርት መሠረተ ልማት መስፋፋት በተለይም ለሱስ ተጋላጭ የሆኑ ወጣቶች ከሱስ እንዲርቁ ለማድረግ ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡ በተጨማሪም የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ለበርካታ ወጣቶች የሥራ እድልም እየፈጠሩ ሲሆን ይሄም የወጣቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ሆኗል፡፡

በመዲናዋ የተገነቡት ዘመናዊ የስፖርት ማዕከላት የከተማዋን ውበት ከመቀየር ባሻገር አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የስፖርት ኩነቶችን፣ ውድድሮችንና ጉባኤዎችን ለማስተናገድም ያስችላሉ።

በከተማዋ እየተስፋፋ ያለው የስፖርት መሠረተ ልማት ብቁ እና ተወዳዳሪ ስፖርተኞችን ለማፍራት መሰረት እየጣለ ሲሆን የከተማዋን የስፖርት ቱሪዝም ገቢም የሚያሳድግ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የቄራ አልማዝዬ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

በቄራ አልማዝዬ ሜዳ ምርቃት ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ከአምስት ዓመት በፊት የተደረገለት እድሳት በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ ማሻሻያዎችን በማድረግ የቄራ አልማዝዬ ሜዳ እና ስልጠና ማእከል በዘመናዊ መልኩ ተገንብቶ ለስፖርት ቤተሰቡ እና ለወጣቶች መበርከቱን ገልጸዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያ መሰረተ ልማቶችን እንደገነባ እና የስፖርት መሰረተ ልማት ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከንቲባዋ አመላክተዋል፡፡

የሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review