ከተማ አስተዳደሩ የዜጎችን ሰብአዊ ክብርና ማህበራዊ ደህንነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን እየሰራ ነው

You are currently viewing ከተማ አስተዳደሩ የዜጎችን ሰብአዊ ክብርና ማህበራዊ ደህንነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን እየሰራ ነው

AMN-ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህብረተሰቡ፣ ከባለሀብቶች እና ከበጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር የሚያካሂዳቸው የቤቶች ልማትና የማህበራዊ ድጋፍ ስራዎች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የዜጎችን ሰብአዊ ክብር የሚመልሱ ታሪካዊ ምዕራፎች ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የተገነባውን የበጎነት መኖሪያ ሕንፃ ለአቅመ ደካሞችና ለሀገር ባለውለታዎች አስረክበዋል።

በከንቲባዋ ተመርቆ ለተጠቃሚዎች የተላለፈው አዲስ የመኖሪያ ቤት ነዋሪዎች ቀደም ሲል ያሳልፉት የነበረውን አስቸጋሪ ሕይወት በአዲስ ምዕራፍ የለወጠ ነው።

ቀደም ሲል እናቶች በውሃ፣ በመጸዳጃ ቤት እና በሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች እጥረት ምክንያት ይደርስባቸው የነበረው ከፍተኛ መከራ ተቀርፎ፣ አሁን ላይ በንጹህ እና ሰብአዊ ክብራቸው በተጠበቀ አግባብ መኖሪያ ቤት ማግኘት መቻላቸው ትልቅ ታሪካዊ ለውጥ መሆኑ ተመላክቷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፤ ቤት ማግኘት ብቻ ሳይሆን ክብሩ በተጠበቀ መንገድ መኖር ለእያንዳንዱ ዜጋ ይገባዋል ያሉ ሲሆን መንግስት የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

አክለውም፤ የነዋሪዎችን የኑሮ ሁኔታ የበለጠ ለማሻሻል፣ የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ እንዲሁም ህጻናትንና ቀጣይ ትውልድን ታሳቢ ያደረገ ዘላቂ የከተማ ልማት የመገንባት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በትብብር መስራት ለሁሉም ወገን ዘላቂ ጥቅም የሚያስገኝ መሆኑን የገለጹት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማዋ ባለሀብቶችና በጎ ፈቃደኞች በከተማ አስተዳደሩ ማህበራዊና ልማታዊ ስራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

በትዝታ መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review