አዲሱ የመኖሪያ ቤት የልጆቻችንንና የቤተሰባችንን የአእምሮ እረፍትና ደስታ መልሷል- የቤት ግንባታ ተጠቃሚዎች

You are currently viewing አዲሱ የመኖሪያ ቤት የልጆቻችንንና የቤተሰባችንን የአእምሮ እረፍትና ደስታ መልሷል- የቤት ግንባታ ተጠቃሚዎች

AMN- ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የተገነባውን የበጎነት መኖሪያ ሕንፃ ለአቅመ ደካሞችና ለሀገር ባለውለታዎች አስረክበዋል፡፡

በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ለተጠቃሚዎች በተላለፈው አዲስ የመኖሪያ ቤት ልማት እፎይታን ያገኙ ነዋሪዎችም፤ የቀደመው አስቸጋሪ ሕይወታቸው በአዲስ ተስፋ መተካቱን ገልጸዋል።

የቤት ግንባታ ተጠቃሚ የሆኑት አቶ ካሣሁን ዓለሙ ቀደም ሲል በነበረባቸው አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ልጆቻቸው የገጠሟቸውን ተግዳሮቶች ሲያስታውሱ፤ በቀደመው ቤታችን ሕፃናት ልጆቻችን የመፀዳጃ ቤት አገልግሎት ለማግኘት የሚደርስባቸው እንግልትና ጭንቀት ለከፍተኛ ሥነ-ልቦናዊ ጉዳት ይዳርጋቸው ነበር ብለዋል።

አሁን ግን ከነበሩበት የጭንቅና የትግል ሕይወት ወጥተው ሰፊ ሳሎን፣ ዘመናዊ ኩሽና እንዲሁም የሻወርና የእጅ መታጠቢያ ሲንክ ያሟላ ደረጃውን የጠበቀ አዲስ መኖሪያ ቤት በማግኘታቸው የልጆቻቸውም ሆነ የቤተሰባቸው የአእምሮ እረፍትና ደስታ መመለሱን መናገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የአቶ ካሣሁን አለሙ ባለቤት ወ/ሮ ዕፁብወርቅ ደምለው በበኩላቸው፤ ቤቱ ከዛሬ ነገ በላያችን ላይ እንዳይፈርስ ሁልጊዜ እሰጋ ነበር ሲሉ የቀደመውን የዕለት ተዕለት ሥጋታቸውን አስታውሰዋል፡፡

ዛሬ ላይ የፈራረሰ መኖሪያና የተጎሳቆለ አካባቢ ሙሉ በሙሉ በአዲስ ተቀይሮ፣ ለሰው ክብር የሚመጥን ዘመናዊ ሕንፃ ተገንብቶ በመሰጠቱ የተሰማቸውን ደስታም ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review