“የአደይ ኮንቴምፖራሪ አርት አዋርድ” አዲስ አበባ ዘመናዊ ጥበብን ለማሳደግ እና የአርቲስቶችን የፈጠራ አቅም ለማበረታታት ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው

You are currently viewing “የአደይ ኮንቴምፖራሪ አርት አዋርድ” አዲስ አበባ ዘመናዊ ጥበብን ለማሳደግ እና የአርቲስቶችን የፈጠራ አቅም ለማበረታታት ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው

AMN- ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም

በዓድዋ ድል መታሰቢያ የተካሄደው “አደይ ኮንቴምፖራሪ አርት አዋርድ” አዲስ አበባ ዘመናዊ ጥበብን ለማሳደግ፣ የአርቲስቶችን የፈጠራ አቅም ለማበረታታት እና ከተማዋን ተመራጭ ዓለም አቀፍ የባህልና የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው።

መድረኩ በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ዘርፎች ለላቀ ሥራ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን ያከበረና ለፈጠራ ሥራቸው እውቅና የሰጠ ታሪካዊ መድረክ ሆኗል።

የአዋርዱ መሥራችና የጥበብ ዳይሬክተር እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰርከስ ፕሬዚዳንት አርቲስት ተክሉ አሻግሬ፤ የሽልማት መድረኩ ከተጠነሰሰበት ጊዜ አንስቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ያልተቋረጠ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አስተዳደሩ የኪነ-ጥበብን ዘርፍ ለማሳደግና አርቲስቶችን ለማበረታታት እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነትም አድንቀዋል። ዝግጅቱ አዲስ አበባ ዘመናዊ ጥበብን ለማሳደግ፣ የአርቲስቶችን የፈጠራ አቅም ለማበረታታት እና ከተማዋን ተመራጭ ዓለም አቀፍ የባህልና የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው።

“የአደይ ኮንቴምፖራሪ አርት አዋርድ”መርሐ ግብርን የትውልድ ድምጽ የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሁሉም የሚዲያ አማራጮቹ በቀጥታ አሰራጭቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review