በትውልድ ሥነ-ምግባር ግንባታና ሙስናን በመከላከል ረገድ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ

You are currently viewing በትውልድ ሥነ-ምግባር ግንባታና ሙስናን በመከላከል ረገድ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ

AMN – ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም

በትውልድ የስነ ምግባር ግንባታ እና የሙስና መከላከል ስራዎችን ውጤታማ ተግባራት ለማከናወን ቅንጅዊ ስራዎች ላይ ማተኮር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ገለጸ።

ኮሚሽኑ የፀረ -ሙስና ትግልን ለማጠናከር እና ብልሹ አሰራሮች ለማስቀረት አዲስ ሚዲያ ኔትወርክን ጨምሮ ከ13 ባለድርሻ ተቋማት ጋር ውይይት እያተካሄደ ነው።

በትውልድ የስነ ምግባር ግንባታ እና የሙስና መከላከል ስራዎችን ውጤታማ ተግባራት ለማከናወን ቅንጅዊ ስራዎች ላይ ማተኮር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጀማል ረዲ ገልጸዋል።

ባለፉት 3 እና 4 ዓመታት በሙስና የተገኘ ሀብትን ማስመለስ ብቻ ሳይሆን፣ ቀድሞ መከላከል ላይም በርካታ ስራዎች መስራት መቻሉን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ይህንን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል።

ሙስና ማንኛውንም አይነት ማህበራዊ መሰረት ሳይመርጥ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ፣ በመከላከል እረገድ ሁሉም ዜጋ ተሳታፊ መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡

ኮሚሽኑ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክን ጨምሮ ከ13 ተቋማት ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራርሟል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review