የአየር ንብረት ፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋትና የታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ቅድሚያ ተግባራቸውን መደገፍ ይገባል – ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

You are currently viewing የአየር ንብረት ፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋትና የታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ቅድሚያ ተግባራቸውን መደገፍ ይገባል – ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

AMN- ኅዳር 2/2019 ዓ.ም

የአየር ንብረት ፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋት እና የታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ቅድሚያ ተግባራቸውን መደገፍ እንደሚገባ የገንዘብ ሚኒስትርና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገለፁ።

ከCOP31 ጎን ለጎን “ባለብዙ ወገን የአየር ንብረት ፈንዶች፡ ለተሻለ ተደራሽነትና ለላቀ ተጽዕኖ በጋራ መሥራት” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ መድረክ ላይ የገንዘብ ሚኒስትርና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም፤ ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋት፣እንዲሁም የታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ቅድሚያ ተግባራቸውን መደገፍ ይገባል ብለዋል።

በዚህ ረገድም የባለብዙ ወገን የአየር ንብረት ፈንዶችን ውጤታማነት ማሳደግ ያለውን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review