AMN – ኅዳር 4/2019 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ በዘላቂነት ለመመለስ በትጋት እንደሚሠራ አስታወቁ፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ራዕይ መነሻ በማድረግ፣ በመዲናዋ የነዋሪዎችን አቅም ያገናዘበና የተለያዩ አማራጮችን ያካተተ የቤት ግንባታ መርሐ ግብር እየተተገበረ ይገኛል።
በከተማ አስተዳደሩ በጀት፣ በግለሰቦች፣ በመንግሥትና በግል አጋርነት እንዲሁም በማኅበራት ተደራጅተው የሚሠሩ የቤት አቅርቦት አማራጮች ተቀርጸው ወደ ተግባር መገባቱንም ከንቲባዋ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ብቻ በአንድ ዓመት ውስጥ 100 ሺህ ቤቶችን ማስጀመር መቻሉ በከተማዋ ታሪክ የመጀመሪያው ክስተት መሆኑን አንስተዋል።

በ21 ሳይቶች በመገንባት ላይ ከሚገኙት 100 ሺህ ቤቶች መካከል 50 ሺህ ያህሉ በከተማ አስተዳደሩ በጀት፣ ቀሪዎቹ 50 ሺህ ደግሞ በመንግሥትና በግል አጋርነት እንዲሁም በማኅበራት እየተገነቡ እንደሚገኙ ከንቲባዋ አብራርተዋል፡፡
በበረከት ጌታቸው