የገንዘብ ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ዘርፍ መሪዎች ጋር መከሩ

You are currently viewing የገንዘብ ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ዘርፍ መሪዎች ጋር መከሩ

AMN – ኅዳር 5/2019 ዓ.ም

የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ዘርፍ መሪዎች ጋር የውይይት መድረክ መርተዋል። ።

ውይይቱ ወደ COP32 ጉባኤ በሚደረገው ጉዞ ላይ በአጋርነትና በድጋፍ ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር።

ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት COP32 ለብዙ ወገኖች ትብብር ወሳኝ ዕድል መሆኑን አንስተው፣ የአየር ንብረት ጥበቃ እርምጃዎችና ልማት በተቀናጀ መንገድ ሊተገበሩ እንደሚገባ አጉልተው ገልጸዋል።

ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እስካሁን ድጋፍ እያደረጉ ላሉ አጋሮች ምስጋናቸውን አቅርበው፤ የበጎ አድራጎት ዘርፉ ከጉባኤው ዝግጅት ባለፈ የድርድር ውጤቶችን ወደ ተግባራዊ እርምጃዎችና የኢንቨስትመንት ዕድሎች በመቀየር በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የበጎ አድራጎት ዘርፍ መሪዎችም በበኩላቸው የኢትዮጵያን ቅድመ ዝግጅት አድንቀው፤ ለCOP32 ፕሬዚዳንትነት አመራር ድጋፍ ለማድረግና በሂደቱ በትብብር ለመሳተፍ ያላቸውን ጽኑ ዝግጁነት ገልጸዋል።

#COP32#Ethiopia#ClimateAction

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review