AMN ህዳር 20/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከጣሊያኑ ዩኒቨርስቲ ዲ ናፖሊ ሎሪያንታሌ ጋር በትምህርት ዘርፍ አብሮ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
የመግባቢያ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረ/ፕ/ር) እና ከዩኒቨርስቲ ዲ ናፖሊ ሎሪያንታሌ ሮቤርቶ ዩቶሊ (ፕ/ር) ተፈራርመዋል።
የስምምነቱ ዓላማ በተቋማቱ መካከል ትምህረታዊ ትብብርን፣ የጋራ ግንኙነትንና መግባባትን ማዳበርና አብሮ ለመስራት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
እንዲሁም በተለያዩ መስኮች ሁለንተናዊ ትብብር ማጠናከር የሚያስችል ስምምነት እንደሆነም መገለጹን ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡