ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት የሰላም ስምምነት ፈፅመው በምክክር መድረኩ እንዲሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን-ጃል ሰኚ ነጋሳ

You are currently viewing ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት የሰላም ስምምነት ፈፅመው በምክክር መድረኩ እንዲሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን-ጃል ሰኚ ነጋሳ

AMN-ታህሣሥ 13/2017 ዓ.ም

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሰራዊት አባላት በሀገራዊ ምክክሩ እየተሳተፉ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የዜጎችን ሰላም ለማስፈን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ምክክር አስፈላጊ መሆኑን በኦሮሚያ ክልል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሰራዊት አባላት ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ ከመንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረመው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሰራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ የምክክሩን አስፈላጊነት አፅንኦት ሰጥቶ፣ የኦሮሞ ህዝብም ምክክሩ ሰላም ያመጣል የሚል እምነት እንዳለው ገልጿል፡፡

ምክክሩ ምሉዕ የሚሆነው ሁሉም ዜጋ ሲሳተፍበት መሆኑን የተናገረው አመራሩ ለዚህም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሁሉ እንደነሱ የሰላም ስምምነት ፈፅመው በዚህ የምክክር መድረክ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

“በምክክር መድረኩ ሃሳቦችን በነፃ አንስተን፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከራክረን፣ ለዜጎች ሰላምና ደህንነት የሚጠቅሙ ሀሳቦችን ይዘን ስንወጣ ነው ምክክሩ የተሳካ የሚሆነው ያለው” ጃል ሰኚ ነጋሳ “ለዚህም ሁላችንም ለምክክሩ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል” ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይህንን የምክክር መድረክ በማመቻቸቱ ምስጋና ማቅረቡን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review