በእስራኤልና በሊባኖስ መካከል የተደረገዉ የተኩስ አቁም ስምምነት ከኢራን ጋር ለሚደረገው የሰላም ስምምነት መንገድ የሚከፍት ነው

You are currently viewing በእስራኤልና በሊባኖስ መካከል የተደረገዉ የተኩስ አቁም ስምምነት ከኢራን ጋር ለሚደረገው የሰላም ስምምነት መንገድ የሚከፍት ነው

AMN- ሚያዝያ 09/2018 ዓ.ም

በሊባኖስ እና በእስራኤል መካከል የተደረገው የ10 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ከትላንት ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል፡፡

ስምምነቱን ተከትሎ በቤይሩት የተለያዩ አካባቢዎች ህዝቡ ደስታዉን በመግለጽ ላይ የሚገኝ ሲሆን ለግማሽ ሰዓት ያህል በደስታ የተተኮሱ የሮኬት ፍንዳታ ድምፆች ይሰሙ እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል።

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ቀጣዩ ስብሰባ ቅዳሜና እሁድ ሊካሄድ እንደሚችል የገለጹ ሲሆን ፤ ይህም የኢራን ጦርነት ወደ ማብቂያው እየተቃረበ ነው የሚለውን ተስፋን እያጠናከረ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

የቴህራን የኑክሌር ፍላጎት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በኢስላማባድ በተካሄደው ድርድር ላይ አወዛጋቢ ነጥብ ሆኖ የቆየ ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ኢራን ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት እና ከዚያ በላይ የኑክሌር መሣሪያ ላለመያዝ ቃል ገብታለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ከሆነ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ በጣም ተቃርበናል፤ ጦርነቱ በቅርቡ ሊያበቃ ይገባል ብለዋል።

በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት የጀመረው የኢራን ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል፤ የነዳጅ ዋጋ እንዲንር በማድረግም ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትልቅ የፖለቲካ ራስ ምታት ሆኖባቸዋል።

የሊባኖሱ የተኩስ አቁም ከኢራን ጋር ለሚደረግ ሰፊ የሰላም ስምምነት መንገድ የሚከፍት ከሆነ፣ እስካሁን ስልታዊ ጠቀሜታ ያለውን የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ለመክፈትና ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት እንዳትሆን ለማገድ ለሚታገለው ለትራምፕ አስተዳደር ትልቅ ድል እንደሚሆን ሮይተርስ አስነብቧል።

ይሁን እንጂ የተኩስ አቁሙ አሁንም ስጋት እንዳለበት እየተነገረ ይገኛል፡፡

የሊባኖስ ጦር ፣ እስራኤል የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ በተለያዩ የደቡብ ሊባኖስ መንደሮች ላይ አልፎ አልፎ የመድፍ ድብደባ በመፈጸም ስምምነቱን ጥሳለች ቢልም ጉዳዩን አስመልክቶ ከእስራኤል

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review