AMN ሚያዝያ 27/2018 ዓ.ም
አዲሱ ትዉልድ የባህር በር ጥያቄን በመመለስ አርበኝነቱን ሊያረጋግጥ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ተናገሩ።
85ኛው የዐርበኞች የድል በዓል አራት ኪሎ በሚገኘዉ የአርበኞች መታሰቢያ ሐውልት እየታሰበ ይገኛል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉትየኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፤ አንድነታችንን ካጠናከርን ኢትዮጵያ ከዚህ በላይ ከፍ እንደምትል እያየን ነው ያሉ ሲሆን በአርበኞች የድል በዓል የሚታሰበዉ የኢትዮጵያዊያን የድል ገድል ነው ብለዋል።
አዲሱ ትዉልድ ታሪክ መስራት፣ ታሪክን ማወቅና መጠበቅን ይጠበቅበታል ያሉት የማህበሩ ፕሬዝዳንት የሀገር ኩራት የሚሆኑ ታሪኮችን ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የአርበኞች የድል በዓል እንዲህ ባለ መልኩ ተከብሮ አያውቅም ያሉት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ከተማ አስተዳደሩ ቀኑን ልዩ በሆነ መልኩ እንዲከበር አድርጎል ብለዋል።
ያለፍትህ እና ያለአግባብ ያጣነው የባህር በር የህልውና እና የመብት ጉዳይ ነው ያሉ ሲሆን አዲሱ ትዉልድ የባህር በር ጥያቄን በመመለስ አርበኝነቱን ሊያረጋግጥ ይገባል ብለዋል፡፡
በትዝታ መንግስቱ