የድህነታችን ቋጠሮ የሚፈታው ሁላችንም በርትተን ስንሰራ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የድህነታችን ቋጠሮ የሚፈታው ሁላችንም በርትተን ስንሰራ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም

የድህነታችን ቋጠሮ የሚፈታው ሁላችንም በርትተን ስንሰራ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ ዛሬ ለ1278 ኢንተርፕራይዞች የስራ መስሪያ ቦታ ሼዶች አስተላልፈናል ብለዋል። በዚህም 3889 እንቀሳቃሾች ተጠቃሚ ሆነዋል።

በዚህ አመት ከ10ሺህ የሚደርሱ መስሪያ ቦታዎችና ሼዶች በፍጥነትና በጥራት ገንብተን ያስተላለፍን ሲሆን ዛሬ ያስተላለፍናቸዉ አብዛኛውቹ ከ3ወር ባልበለጠ ጊዜ ተገንብተው ለተጠቃሚዎች የተላለፏ ናቸው።

በከተማችን የስራ ባህል እንዲቀየር ለስራ የሚተጋ ፥ በግል ጥረት ራስን መቻል እና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የማያቋረጥ ሥራ እየሰራን ነው ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች ችግሮችን ብቻ በማውራት ከድህነት መላቀቅ አይቻልም፤ ከድህነት ለመላቀቅ በተገኘው እድል እልህ ውስጥ ገብተን ስንሰራ ብቻ ነው ያሉ ሲሆን ድህነትን የሚፈተው በመንግስታ ብቻ አይደለም ይልቁንም የሁላችንም ጥረት ይጠይቃል ነው ያሉት፡፡

ዛሬ የመስሪያ ቦታ ያገኛችሁ በልቶ ለማደር ብቻ ሳይሆን ከመንግሥት ያገኛችሁት ድጋፍ ተጠቅማችሁ እልህ ውስጥ ገብታችሁ ተግታችሁ በመስራት የትላልቅ ኩባንያ ባለቤት እንድትሆኑ ይጠበቃልም ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች፤ ተደራጅታችዃ፥ ሰልጥናችዃል በጋራ ለማደግ በጋራ ለመለወጥ ለሀገር እድገም የበኩላችሁ አስተዋፅዖ ማበርከት እንድትችሉም አደራ እላለሁ፡፡ የሚሰሩ እጆችን እናበረታታለን ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review