AMN- ግንቦት 10/ 2018 ዓ.ም
”የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ሀገራዊ ጉባኤ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
ኢትዮጵያ የልማት ትልሞቿን እንዲሁም ስኬቶቿን በመረጃ እና በአሃዛዊ ማስረጃ መሰነድ ከጀመረች ሰነባብታለች። ይህ እርምጃ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በሌሎች በሚደገፉና በተበታተኑ የመረጃ ቋቶች ላይ የነበራትን ሙሉ ጥገኝነት ለመቅረፍ ያሳየችውን ከፍተኛ ቁርጠኝነት ማረጋገጫ ነው።

ይህ አዲስ ምዕራፍ የሀገሪቱን የመረጃ ሉዓላዊነት በተግባር በማረጋገጥ፣ ኢትዮጵያ በራሷ መረጃ ላይ ተመስርታ እንድትወስንና የራሷን የልማት መስመር እንድትተልም አስችሏታል።
በዚህም መሠረት፤ በዛሬው ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ልማትና የመረጃ ሉዓላዊነት ጉዞ ያመጣቸው ስኬቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች በጥልቀት እንደሚዳሰሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡